የእንቅልፍ ሰዓትዎን እንዴት ማስተካከል እንደሚችሉ ያውቃሉ?

እንቅልፍ ላይ ያለች ሴት Image copyright Getty Images

ሰዎች የተለያየ የእንቅልፍ ሰዓት አላቸው፤ አንዳንዶች በጊዜ ተኝተው በማለዳ መንቃትን ያዘወትራሉ። ሌሎች ደግሞ ሌሊቱን ገፍተው ሲነጋ እንቅልፍ የሚጥላቸው አሉ። እርስዎ የትኛው ልምድ ነው ያለዎት? የማለዳ ወፍ ወይስ የሌሊት ወፍ?

የእንግሊዝና የአውስትራሊያ ተመራማሪዎች የእንቅልፍ ሰዓትን በማስተካከል የአካልና የአዕምሮ ጤንነትን መጠበቅ እንደሚቻል እንደደረሱበት ይፋ አድርገዋል። አጥኚዎቹ ትኩረት ያደረጉት ሳይተኙ እኩለ ሌሊቱን የሚገፉ 'የምሽት ሰዎች' (የሌሊት ወፎች) ላይ ነው።

ስለ እንቅልፍ የተሳሳቱ አመለካከቶች

የኢትዮጵያን አደራዳሪነት የሱዳን ህዝብ እንዴት ይመለከተዋል?

በንቅለ ተከላ ዕይታው የተመለሰለት ኢትዮጵያዊ ታዳጊ

ባለሙያዎቹ እንደሚሉት ጥናቱን ለማካሄድ ውስን የእንቅልፍ ሰዓት መስጠትን፣ አነቃቂ መጠጦችን ማስወገድና የጠዋት ፀሐይ መኮምኮም የተጠቀሟቸው ዘዴዎች ናቸው።

ዘዴዎቹ የተለመዱ ቢሆንም በሰዎች ሕይወት ላይ ግን ከፍተኛ ልዩነት ማየት የተቻለበት ነበር ብለዋል።

እያንዳንዱ ሰው የፀሐይን መውጣትና መግባት ተከትሎ የራሱ የእንቅልፍ ሰዓት አቆጣጠር አለው። ለዚህም ነው ሲመሽ እየተኛን፤ ሲነጋ የምንነቃው። ይሁን እንጂ ይህ ለሁሉም ሰው ላይሰራ ይችላል፤ ምክንያቱም የአንዳንድ ሰዎች ሰዓት ከሌሎቹ ዘግይቶ ይዘውራልና።

እንቅልፍ እንዲህ ጠቃሚ ነገር ኖሯል?

በማለዳ ዝማሬያቸውን እንደሚያሰሙት 'የማለዳ ወፎች' ሁሉ የጠዋት ሰዎች በማለዳ ነው የሚነቁት ግን ማታ ለማምሸት ይቸገራሉ፤ በተቃራኒው የማታ ሰዎች (የሌሊት ወፎች) ምሽቱን ንቁ ሆነው ይገፉና ጠዋት ላይ ግን እንቅልፍ ያሸንፋቸዋል።

ለምሽት ሰዎች (የሌሊት ወፎች) በጣም አስቸጋሪው ነገር ከምሽቱ 3፡00 እስከ ማለዳ 11፡00 ባሉት ሰዓታት ራሳቸውን ማስማማት ነው። የጠዋቱ የማንቂያ ደወል ሰውነትዎ ከመዘጋጀቱ አንድ ሰዓት ቀድሞ ያነቃዎታል። ይህም ከከፍተኛ የጤና ችግር ጋር ይያያዛል።

ተመራማሪዎች ጥናት ባደረጉባቸውና በአማካይ ወደ መኝታቸው ለመሄድ እስከ ሌሊቱ 8፡30 የሚቆዩና እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ከእንቅልፋቸው የማይነቁ 21 የማታ ሰዎች (የሌሊት ወፎች) ላይ ጥናት አድርገዋል።

በጥናቱ የተመረጡት ሰዎችም የሚከተሉትን እንዲፈፅሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር።

• ሁል ጊዜ ከእንቅልፋቸው ከሚነቁበት ሰዓት ሁለት ወይም ሦስት ሰዓት ቀድመው እንዲነሱና የጠዋት ፀሐይ እንዲሞቁ ማድረግ

• በተቻላቸው መጠን ቁርሳቸውን እንዲመገቡ

• የጠዋት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ

• በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት ምሳቸውን እንዲመገቡና ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት በኋላ ምንም ዓይነት ምግብ እንዳይመገቡ

• የሚያነቃቁ መጠጦችን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በኋላ እንዳይጠቀሙ

• ከቀኑ 10 ሰዓት በኋላ ምንም ዓይነት 'ሸለብታ' (ናፕ) እንዳያደርጉ

• የብርሃን መጠኑ በተወሰነበት ክፍል ከተለመደው የእንቅልፍ ሰዓት ሁለት ወይም ሦስት ሰዓት ቀድመው እንዲተኙ እና

• የሚተኙበትንና የሚነቁበትን ሰዓት ተመሳሳይ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር።

ከሦስት ሳምንታት በኋላ፤ ሰዎቹ የመኝታ ሰዓታቸውን ከተለመደው በሁለት ሰዓት ማስተካከል ችለው እንደነበር የበርሚንግሃም፣ ሱሬይ እና ሞናሽ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ውጤት አመልክቷል።

ደስታና እንቅልፍ- የፀሃይ ብርሃን ለህይወት አስፈላጊ የሆነባቸው ምክንያቶች

የጥናት ውጤቱ እንዳሳየው ሰዎቹ ዐይናቸውን የሚከድኑበት ሰዓት ተመሳሳይ ነበር፤ ነገር ግን ዝቅተኛ በሆነ ደረጃም ቢሆን እንቅልፍ ማጣት፣ ጭንቀትና ድብርት አጋጥሟቸዋል። የሚነቁበት ሰዓት ግን መሻሻል አሳይቷል።

"ተራና የተለመዱ የሆኑ ሥራዎችን መልክ ማስያዝ፤ የሚያመሹ ሰዎች (የሌሊት ወፎች) የእንቅልፍ ሰዓታቸውን እንዲያስተካክሉ ረድቷቸዋል፤ የአካልና የአዕምሮ ጤንነታቸውም ተሻሽሏል" ይላሉ በሰሬይ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ደብራ ኬኔ።

እርሳቸው እንደሚሉት በቂ ያልሆነ እንቅልፍ እና የእንቅልፍ ሰዓት መዛነፍ የሰውነትን ጤናማ ተግባር ያውካል፤ ለልብ በሽታ፣ ለካንሰርና ለስኳር በሽታም ያጋልጣል።

ሰውነታችን ለተለመደው ጤናማ ተግባሩ የሚያስፈልገውን የፀሐይ ሙቀት ማግኘት አለበት። በመሆኑም ሰውነትን ለማታ ፀሐይ ከማጋለጥ ይልቅ ለጠዋት ፀሐይ ማጋለጥ ይመከራል።

ጥናቱ እንደሚያስረዳው የተዛባ የመተኛና የመንቂያ ሰዓት ካለን የሰውነታችንን ውስጣዊ ሰዓት (ሰርካዲያን ሪትም) የመተኛና የመንቂያ ሰዓታችን እንዲዛባ ያደርገዋል።

በመሆኑም ይህን ተፈጠዕሯዊ ሰዓት ለማስተካከል የተጠቀምናቸው ዘዴዎች የተለመዱ ሊመስለዎት ቢችልም ሰውነታችን ሰዓቱን እንዲለማማድ ስለሚያስችለው የእንቅልፍ ሰዓታችንንም ለማስተካካል ይረዳል ።

"አንፃራዊ በሆነ መልኩ እነዚህን ልምምዶች ማድረግ በጣም ቀላሉና ለውጥ የሚያስገኝ ነው፤ ይህ ለእኔም በጣም አስደንቆኛል" ብለዋል የበርሚንግሃም ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር አንድሪው ባግሻው።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ